ስለእኛ ለማወቅ

Location
ሙስሊሞት በጸሎት ላይ
ሙስሊሞት በጸሎት ላይ

ተልዕኮችን፡ 

የወንጌል መልዕክት በአፍሪካ ቀንድ ዙሪያ ላሉ ህዝቦች በቋንቋቸው ሊደርሳቸው በሚችል አማራጭ ሁሉ፣ ትርጉም በሚሰጥ መልክ ማቅረብ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ቃሉን ሰምተው፣ በክርስቶስ በማመን የእርሱ ደቀመዝሙር በመሆን እግዚአብሔር ያሰበላቸውን በረከት እንዲለማመዱ ማገዝ ነው፡፡ 

የቡና ባህል
የቡና ባህል

ራዕያችን፡

በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያሉ ሰዎች የክርስቶስ ማዳን በማወቅ፣ በጸጋው በመታደስ፣ ለዘላለም መንግስቱ ተዘጋጅተው ማየት፣ 

በእምነትና በመታደስ ዘላቂ የሆነ መንፈሳዊ ተጽዕኖ በመፍጠር በአፍሪካ ቀንድ የእግዚአብሔር መንግስት ሲሰፋ ማየት፡፡ 

የድሮ የራድዮ ቢሮ

ታሪካችን፡ 

  • በ1972 ዓ.ም. ነበር፣ የኤስ አይ ኤም ካውንስል፣ ወንጌል ለማሰራጨት ለአማኞች የወንጌል ትምህርት ለማስተማር ቤተክርስቲያንን ለማጠናከር የራድዮ አግለግሎት መጠቅም አለብን የሚል ደፋር ውሳኔ የወሰነው፡፡ በዚያ ዘመን ከመንግስት ለውጥና ፖለቲካው ይከተለው ከነበረው ርዕዮት ዓለም የተነሳ ወንጌል በግልጽ ለብዙዎች መንገር አስቸጋሪ በመሆኑ፣ ራድዮ ለብዙዎች የተስፋ ብርሃን ይዞ መጣ፡፡
  • ካውንስሉ ውሳኔ ባስተላለፈ ቀጣይ ዓመት፣ ፖል ኤንትዝ የተባሉ የኤስ አይ ኤም ሚስዮናዊ ከእርሳቸው ጋር እንዲሰራ ከመረጡት ቡድን ጋር በአማርኛ ቋንቋ ከናይሮቢ ሆነው መልዕክት ማዘጋጀት ጀመሩ፡፡ እነዚያም የተዘጋጁ መልዕክቶች ይሰራጩ የነበረው በፊባ ራድዮ ሲሸልስ ከሚገኘው ጣቢያ ነበር፡፡ ስርጭቱም በአጭር ሞገድ በመሆኑ፣ ብዙ ለወንጌል ዝግ የሆኑ ቦታዎች ስንኳ ወንጌል ለማድረስ ያስቻለ ነበር፡፡
  • በአስፈላጊነቱ ታምኖበት የተጀመረው የራድዮ አገልግሎት በአጭር ጊዜ ውስጥ፣ በአፍሪአክ ቀንድ አካባቢ ላሉ በወንጌል ላልተደረሱ ህዝቦች የሕይወት መንገድ የሚሳይ፣ በስደት ውስጥ የነበሩትን የሚያበረታታ፣ ለብዙዎች መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚያቀርብ አገልግሎት ሆነ፡፡
  • የደርግ መንግስት መውደቅ ተከትሎ፣ በ1985 ዓ. ም. ፖል ኤንትዝ ከእርሳቸው ጋር የሚሰራ ቡድን በማቋቋም አገልግሎቱን በስፋት ጀመሩ፡፡
  • በ1988 ዓ.ም. የጉራጊኛ ቋንቋ በመጨመር አገልግሎቱ እየተስፋፋ ሄደ፡፡ የጉራጊኛ ቋንቋ ፕሮግራም ለህዝቡ በራድዮ መምጣቱ ለወንጌል ሩቅ የነበረውን ማህበረሰብ ለመድረስ አይነተኛ መሳሪያ ሆነ፡፡
  • የሶማሊኛ ቋንቋ አገልግሎት ከአማርኛውና ከጉራጊኛው ቀድሞ በ1966 ዓ.ም. አዲስ አበባ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ ከነበረው ፖለቲካ የተነሳ በ1970 ዓ.ም. ወደ ናይሮቢ እንዲዛወር ተደረገ፡፡ ይህንን አገልግሎት የጀመሩት በመሰጠት ብዙ ዋጋ በመክፈል ያገለገሉት እነ አልበርትና ቲና ኢሮን፣ ሩት ማዮርስ፣ ኤሜ አህርን፣ ዋረን ሞዲከርና ማይክል ማድኒ በምስጋና የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
  • ለብዙ ዘመናት የወንጌል መልዕክቶቻችን በፊባ ራድዮ ሲሸልስ፣ ከዚያም ኢብራ በሚያዘጋጃቸው ማሰራጫዎች ለብዙ በወንጌል ላልተደረሱ ህዝቦች ታላቅ ምስክር ሆኖ ቆይቶአል፣ አሁንም ዘመኑ ያመጣቸውን ግኝቶችን ሁሉ በመጠቀም በወንጌል ያለተደረሱ ህዝቦች ለመድረስ በትጋት ላይ እንገኛለን፡፡ እሰከዛሬ የረዳን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡ 
የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ

 

  • ትኩረት አድርገን የምንሰራው፣ የእግዚአብሔር ቃል ለሰዎች በሚገባቸው ቋንቋ በድምጽ፣ በምስልና በድምጽ፣ በጽሁፍ ለታላሚዎቻች ን ሊያደርሱ በሚችሉ መገናኛ መንገዶች፣ በራድዮ፣ በማህበራዊ መገናኛ መንገዶችና ምስልና ድምጽ የሚያጫውቱ መሳሪዎች በመጠቀም ወንጌል ማድረስ ነው፡፡ 

     

  • አጋሮቻችን፣ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያሉ ሰዎች በወንጌል ለመድረስ ሸክሙ ያላቸውና፣ ከኛ ጋር ተመሳሳይ እምነትና እሴት ካላቸው ሁሉ ጋር፣ በአካባቢው ካሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ጋርና፣ ሚስዮናውያን፣ ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ካሉ የወንጌል ስራ ከሚደግፉ ሁሉ ጋር አብረን እንሰራለን፡፡ 

 

  • ጥሪያችን፣ ይህን ታላቅ የሆነውን የወንጌል ዓላማ በጸሎት፣ በአጋርነት፣ በመስጠት እንድትደግፉና እግዚአብሔር በሰጣችሁ ጸጋና እውቀት ወንጌል እንዲሰፋ አብራችሁን እንድትቆሙ ነው፡፡

     

  •   እኛን ለማግኘት ከስር ያለውን እኛ ማግኛ እንዲሆን ያስቀመጥነውን በመንካት መልዕክታችሁ አድርሱን፡፡ እግዚአብሔር ይባርካችሁ፡፡ 

አጋሩ

የእርስዎ ማበረታታ በእጅጉ ይጠቅመናል

የእርስዎ ታሪክ እንዲህ አይነቱን ድረ ገጽ ለመንገባት ያግዘናል